Who's Online

We have 99 guests and no members online

Rate this item
(0 votes)

የዓመታዊ ጉባኤ ጥሪ!

የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማሕበር 30ኛ ዓመታዊ ጉባኤ በአዳማ ከተማ ከረዩ ሂል ሪዞርት ሆቴል ከየካቲት 18 እስከ 20/2011 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡ በዚህ  ጉባኤ በማህበረሰብ ጤና ላይ ያተኮሩ የፓናል ውይይቶችና በርካታ የጥናት ውጤቶች ይቀርባሉ፤ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፡፡ በመሆኑም መላ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ እንዲሳተፉ ማሕበሩ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡

እስከአሁን ያልተመዘገባችሁ ተሳታፊዎች አርብ የካቲት 15/2011 ዓ.ም. ከ2፡30 ጀምሮ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከአዲስ አበባ አዳማ መኪና ስለተዘጋጀ እሁድ የካቲት 17/2011 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት መስቀል አደባባይ በመገኘት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማሕበር!